ከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል

Building The Future
“መጭውን ትውልድ መገንባት”

ራዕይ

ተልዕኮ

እሴቶች

በ2022 ዓ.ም በከፍተኛ ትምህርት የፖሊሲና ስትራቴጂ ምክረ-ኃሳብ በማመንጨት፤ በምስራቅ አፍሪካ ታማኝ የመረጃ ምንጭና የልህቀት ማዕከል ሆኖ ማየት፤

በከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መስክ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ምክረ-ኃሳብ በማቅረብ፤ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ በመንደፍ፤ የአመራርና አስተዳደር አቅም በመገንባት፤ የብቃት ማዕቀፍን በመቅረጽ፤ መንግስትን ማማከርና አስተማማኝ የመረጃ ማዕከል ሆኖ ማገልገል፤

  • ልቆ መገኘት
  • ተፅዕኖ ፈጣሪነት
  • በቡድንመስራት/ አሳታፊነት/ የትብብር መንፈስ
  • ሳይንሳዊ ምክንያታዊነት
  •  የኃሳብ ነጻነት
  • ዘላቂ የትምህርት ልማት

ከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል

የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 351/1995 በ1995 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአዋጅ 650/2001 ዓ.ም እንዲሁም በደንብ ቁጥር 276/2005 የትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል በሚል ስያሜ ሶስቱንም ዘርፎች (አጠቃላይ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እና የከፍተኟ ትምህርት) እንዲያካተት ተደረጎ ሁሉንም ዘርፎች ሲደግፍ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በትምህርትና ስልጠና ስርዓቱ የተደረገውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት የአስፈጻሚ ተቋማትን ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1152/2011 የቀድሞ ስሙን በመያዝ (የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል) የከፍተኛ ትመህርትን እና ቴክኒክና ሙያ በምርምር ላይ መሰረት ያደረገ ተቋማትን የማማከርና የመደገፍ ኃላፊነት የተሰጠው ሲሆን ይህን ተግባሩን ለመፈፀም የጥናትና ምርምር ሥራዎች በስፋት እየሠራ ይገኛል፡፡ 

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያከናውኗቸው የምርምርና የማህበረሰብ አቀፍ ልማት ሥራዎች ልማቱን ሊያቀላጥፉ የሚረዱ መፍትሔ አምጪ ጥናቶች እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ ነው፡፡የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦች ሲያስፈልጉ ጥናት በማጥናት ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱን የማማከር ማዕቀፍ ተሰጥቶታል፡፡ እንዲሁም ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ትግበራ በሚገባባት ጊዜ ተቋማቱ ያላቸውን የአመራር አቅም ለመገንባት የዘርፉን ክፍተቶች በመለየት እንዲሁም መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ሊስፋፉበት የሚችሉበትን ስራ ይሠራል፡፡

የከትስማ ኃላፊነቶች

በወቅታዊ   ጉዳዮች  ላይ ጥናት ና ምርምር   በማካሄድ አማራጭ የፖሊሲ እና ስትራቴጂዎችን ማዘጋጀት ፡፡

ከአለም አቀፍ እና ሃገር አቀፍ ተቋማት ጋር አጋርነት   ትብብርን ያጎለብታል፤የከፍተኛ ትምህርት ጉዳዮችን ከሚያከናውኑ ተመሳሳ ከውጭ አገር አካላት ጋር ግንኙነት ይመሰርታል፤ ዩኒቸቨርሲተዮች የማስተሳሰር እና በመካከለቸዉ አጋረነት የመፍጠር ትልቅ ሚና የመጫወታል ፡፡ አስተማማኝ አገራዊ የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፡፡

የትምህርት እና ስልጠና   ተቋማትን በመደገፍ ስኬታማ እና ዉጤታማ የትምህር እና ስልጠና አስተዳደር ፣ አመራርና ማኔጅመንት መፍጠር ፡፡

ለእያንዳንዱ የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ስለሚሰጥ የጥቅል በጀት ምደባ ሃሳብን ያመነጫል፤ የጥቅል በጀት ምደባ አፈጻጸምን ይከታተላል፤

የትምህርት ስልጠና ጥራትና አግባብነት፣ ተደራሽነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን   ያካሂዳል::

“መጭውን ትውልድ መገንባት”

Building The Future

አጋርነትና ትብብር

Higher Education Strategy Center Ethiopia (HESC)