ስለ ከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል

 1. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እድገት አስመልክቶ ሀገር አቀፍ ስትራቴጂ ያዘጋጃል፡፡
 2. የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት ውስጥ ትመህርትና ምርምር ስለሚጎሎቱ ሁኔታ የረጅም ግዜ ሀገር አቀፍ እቅድ ያዘጋጃል፡፡
 3. የተቋማትን የትምህርትና ምርምር ጥራትን፣ የአካዳሚ ሰራተኞችን ብቃት እንዲሁም የትምህርት ፕሮግራሞችን ለማሳደግ የሚያግዙ አገር አቀፍ መነሻ አሳቦችን ያቀረባል፡፡
 4. በተቋም ደረጃ የሚወጣ እቅድና ስትራቴጂ አገር አቀፍ ደረጃ ከሚወጣው አጠቃላይ የከፍተኛ ትምህርት እቅድና ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ለዚህም ከተቋማት ጋር በቅርበት ይሰራል፣ ስትራቴጂ እቅድ ስምምነትን ይመረምራል፣ ሲፀድቅመ አፈጻጸምን ይከታተላል፡፡
 5. ለእያንዳንዱ የመንግስት ተቋማት ስለሚሰጥ የጥቅል በጀት ምደባን ሃሳብን ያመነጫል፣ የጥቅል በጀት ምደባ አፈፃፀምን ይከታተላል፡፡
 6. የተቋማትን ዓመታዊ የትምህርት፣ የምርምር፣ የፋይናንስና ሌሎች ስታትስቲካዊ መረጃዎችን ይሰበስባል ይተነትናል፣ እንደተገቢነቱም አትሞ ለሚመለከታቸው ያሰራጫል፡፡
 7. ተቋማትን የተለያየ መጠን ባለው የልማት በጀት መልክ የማበረታቻ ሽልማት ስለሚያገኙት መመዘኛና አሰራር ለሚስትሩ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፀድቅም በስራ ላይ ያውላል፡፡
 8. የከፍተኛ ትምህርት ከአገሪቱ አጠቃላይ የማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ፍላጎት ጋር የተጣጣመ መሆኑንና በአካሄዱ ከአለም አቀፍ እውነታ ጋር እኩል የሚራመድ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
 9. ቀልጣፋ የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደር፣ አመራርና ማኔጅመንት እዲኖር ለማድረግ ስለሚቻልበት ሁኔታ ሚኒስቴሩን ያማክራል፡፡
 10. በወቅታዊ የፖሊሲ ጉዳዮች አሰራርና ውጤቶች ላይ ምርምርና ጥናት በማድረግ ትክክለኛ የአሰራር አቅጣጫዎችን ይጠቁማል፣ ለማሻሻያ፣ ለለውጥና ለልማት የእውቀት ግብአት ምንጭ ሆኖ ያገለግላግ፡፡
 11. በአገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ማሻሻያና ልማት ስትራቴጂና እቅድ ላይ ሃሳብ ይሰጣል፡፡
 12. በሃላፊነቱ ማዕከልነት በአገራዊ ተቋማት መካከል ትብብርን ያጎለብታል፣ የከፍተኛ ትምህርት ጉዳዮችን ከሚያከናውኑ ተመሳሳይ የውጭ ሀገር አካላት ጋር ግንኙነት ይመሰርታል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 351/1995 በ1995 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአዋጅ 650/2001 ዓ.ም እንዲሁም በደንብ ቁጥር 276/2005 የትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል በሚል ስያሜ ሶስቱንም ዘርፎች (አጠቃላይ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እና የከፍተኟ ትምህርት) እንዲያካተት ተደረጎ ሁሉንም ዘርፎች ሲደግፍ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በትምህርትና ስልጠና ስርዓቱ የተደረገውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት የአስፈጻሚ ተቋማትን ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1152/2011 የቀድሞ ስሙን በመያዝ (የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል) የከፍተኛ ትመህርትን እና ቴክኒክና ሙያ በምርምር ላይ መሰረት ያደረገ ተቋማትን የማማከርና የመደገፍ ኃላፊነት የተሰጠው ሲሆን ይህን ተግባሩን ለመፈፀም የጥናትና ምርምር ሥራዎች በስፋት እየሠራ ይገኛል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያከናውኗቸው የምርምርና የማህበረሰብ አቀፍ ልማት ሥራዎች ልማቱን ሊያቀላጥፉ የሚረዱ መፍትሔ አምጪ ጥናቶች እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ ነው፡፡የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦች ሲያስፈልጉ ጥናት በማጥናት ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱን የማማከር ማዕቀፍ ተሰጥቶታል፡፡ እንዲሁም ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ትግበራ በሚገባባት ጊዜ ተቋማቱ ያላቸውን የአመራር አቅም ለመገንባት የዘርፉን ክፍተቶች በመለየት እንዲሁም መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ሊስፋፉበት የሚችሉበትን ስራ ይሠራል፡፡

አስተዳደር

ዶ/ር ሀብታሙ ተካ ካባ

ዋና ዳይሬክተር

ዶ/ር ተስፋዬ ሙህዬ እንድሪስ

ም/ዋና ዳይሬክተር (አላማ ፈፃሚ ዘርፍ)

ወ/ሮ ከፈለች ደምቦባ አባሞ

ም/ዋና ዳይሬክተር (አመራርና አስተዳደር ዘርፍ)

Higher Education Strategy Center Ethiopia (HESC)