የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል ጥር/08/2013 የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡

የተቋሙ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም በቀረበበት ወቅት ተቋሙ ባለፉት 6 ወራት ያከናወናቸዉ ተግባራት ዝርዝር የቀረበ ሲሆን በዚህም የሁሉም ስራ ክፍሎች ዝርዝር ተግባራት እና አፈፃፀም፣ የበጀት አጠቃቀም እንዲሁም በጥንካሬ የተሰሩ ስራዎችና በድክመት የተያዙ በተጨማሪም ትኩረት የሚሹ ስራዎች ምን እንደሆኑ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ሃገር በቀል ዕቀዉት የሚለማበት እና የሚመራበት ፖሊስ ምክረ ሃሳብ ፅንሰ ሃሳብ ጥናት እንደተዘጋጀ ተገልጧል፡፡በተጨማሪም በተቋማት የሚዘጋጁ ስታራቴጂያዊ ዕቅዶች ከሃገራዊ ፖሊሲዎች ጋር የሚጣጠሙ መሆናቸዉ የማረጋገጥ ስራ እንደተሰራ እና ይህም ወደ ፊት ጠንክሮ ሊሰራ የሚገባ ስራ እንደሆነ ተገልጧል፡፡

ሌላው ማዕከሉ በታህሳስ ወር ላይ አገር አቀፍ የጥናት ሲምፖዚየም ማዘጋጀቱ የሚታወስ ሲሆን በዚሁም ዕለት ሲምፖዚየው የተሳካ እንዲሆን ተዋቀሩ ኮሚቴዎች ሪፖርት ቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም በጥንካሬ የተሰሩ፣የተጋነነም ባይሆን የነበሩ ክፍተቶችና መልካም አጋጣሚዎችም ቀርበዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ማዕከሉ 12 የሚደረሱ ጥናቶች እንደቀረቡ እና በወቅቱም የተለያዩ ባድርሻ አካላት እንደተሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ይህ ማዕከሉ ባለፉት ስደስት ወራት ካከናወናቸዉ ተግባራት አደኛዉ እንደነበር ተገልጧል፡፡የዚህ ግማሽ አመት አፈፀፃም ጥሩ እደሆነ እና በቀጣይ የቀሪውን ስድስት ወር ዕቅድ በመከለስ ጠንክረን በመስራት ግባቸንን የበለጥ ማሳካት እንደሚቻል የጠቋሙ ዋና ዳይሬክር ዶ/ር ሃብታሙ ተካ ገልፀዋል፡፡

Higher Education Strategy Center Ethiopia (HESC)